ገባዖናዊው ሰማያስ፥ እርሱ በሠላሳው መካከልና በሠላሳው ላይ ኀያል ሰው ነበረ፤ ኤርምያስ፥ ሕዝኤል፥ ዮሐናን፥ ገድሮታዊ ዮዛባት፤
ኢያሱ 15:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቃርም፥ ጋዴርና ሰፈሮችዋ፥ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፤ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻዕራይም፥ ዐዲታይም፥ ገዴራና ገዴሮታይም ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አራት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥ ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፥ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ገባዖናዊው ሰማያስ፥ እርሱ በሠላሳው መካከልና በሠላሳው ላይ ኀያል ሰው ነበረ፤ ኤርምያስ፥ ሕዝኤል፥ ዮሐናን፥ ገድሮታዊ ዮዛባት፤
በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤
የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎችም ተነሥተው እልል አሉ፤ ፍልስጥኤማውያንንም እስከ ጌትና እስከ አስቀሎና በር ድረስ አሳደዱአቸው። የፍልስጥኤማውያንም በድኖቻቸው እስከ ጌትና እስከ አቃሮን በሮች ድረስ በመንገድ ላይ ወደቁ።