ኢያሱ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ “አባቴን እርሻ ልለምነው” ብላ አማከረችው፤ እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባቷ ላይ የዕርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፤ እርሷም ከአህያዋ ወረደች፤ ካሌብም፦ “ምን ፈለግሽ?” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዖትኒኤልም በሠርጋቸው ቀን ዓክሳን ከአባትዋ የእርሻ መሬት እንድትለምን መከራት፤ እርስዋም ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ (መሳ 1፥14 ተመልከት) ካሌብም “ምን ትፈልጊአለሽ” ሲል ጠየቃት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፥ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፥ |
እርስዋም፥ “በረከትን ስጠኝ፤ በደቡብ በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ” አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።
እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ የእርሻ ቦታ ይሰጣት ዘንድ አባቷን እንድትለምነው ጎቶንያል መከራት። እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና አንጐራጐረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድደኸኛል” ብላም ጮኸች። ካሌብም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት።
አቤግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፤ በዳዊትም ፊት በግንባርዋ ወደቀች፤ ምድርም ነክታ ሰገደችለት።