ስለዚህ እነሆ የሞአብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከባኣልሜዎን፥ ከቂርያታይም አደክማለሁ።
ኢያሱ 13:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤተ ፌጎር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤትሲሞት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤተ ፌጎርን፣ የፈስጋን ሸንተረሮችና ቤትየሺሞትን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤተ ፌጎር፥ የፈስጋ ተዳፋት መሬት፥ ቤትየሺሞት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤትፐዖር፥ ከፒስጋ ተራራ በታች ያለው ረባዳ ምድርና ቤትየሺሞት ተብለው የሚጠሩትን ሁሉ ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤተ ፌጎር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤትየሺሞት፥ |
ስለዚህ እነሆ የሞአብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከባኣልሜዎን፥ ከቂርያታይም አደክማለሁ።
ከመካናራ ወሰን ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እርሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረባን፥ ዮርዳኖስንም ሰጠኋቸው።
ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመቱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞሬዎን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅራቢያ ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ፤
በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኬኔሬት ባሕር ድረስ፥ በአሴሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፋስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር የገዛው የአሞሬዎናውያን ንጉሥ ሴዎን፤
የሚሶር ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞሬዎናውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቦቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲዮን የሚኖሩትንም ገደላቸው።