በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ሀገር፥ በጋድ ሀገር፥ የአዴ ልጅ ጌቤር ነበረ፤ በይሁዳም ምድር ላይ እርሱ ብቻውን ሹም ነበረ።
ኢያሱ 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ገደሉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፥ ለጋድም ልጆች፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ባርያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የጌታም ባርያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እነዚህ ሁለት ነገሥታት በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴና በእስራኤል ሕዝብ ጦርነት ድል ሆነው ነበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም ይህን ምድር ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች መቱአቸው፥ የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው። |
በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ሀገር፥ በጋድ ሀገር፥ የአዴ ልጅ ጌቤር ነበረ፤ በይሁዳም ምድር ላይ እርሱ ብቻውን ሹም ነበረ።
ሙሴም፥ “የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች ሁላቸው የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለጦርነት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ።
የጦር መሣሪያችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፤ ከዮርዳኖስም ማዶ የወረስነው ርስት ይሆንልናል” አሉት።
ሙሴም ለጋድ ልጆችና ለሮቤል ልጆች፥ ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞሬዎናውያንን ንጉሥ የሴዎንን መንግሥት፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን መንግሥት፥ ምድሪቱንም፥ ከተራሮችም ጋር ከተሞችን፥ በዙሪያቸውም ያሉትን የምድሪቱን ከተሞች ሰጣቸው።
ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመካከላችሁ እድል ፋንታ የላቸውም፤ ጋድም፥ ሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።”
አሁንም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፤ አሁን እንግዲህ ተመለሱ፤ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።