ኢያሱ 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ ፥ ሜዳውንም፥ በምዕራብ በኩል ያለውንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቆላውን ያዘ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ ያን ምድር በሙሉ፣ ማለት ተራራማውን አገር፣ ኔጌብን ሁሉ፣ የጎሶምን ምድር በሙሉ፣ የምዕራቡን ቈላ፣ ዓረባን እንዲሁም የእስራኤልን አገር ደጋውንና ቈላውን ጠቅልሎ ያዘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ፥ ቈላውንም፥ ዓረባንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቈላውን ያዘ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱ እነዚያን አገሮች፦ ተራራማውን፥ ኔጌብን፥ የጎሼንን ምድር፥ ቈላማውን፥ የዮርዳኖስን ሸለቆ፥ ቈላማውንና ደጋማውን የእስራኤልን ምድር ሁሉ ያዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ፥ ቈላውንም፥ ዓረባንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቈላውን ያዘ፥ |
ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎችንም ያወጣል፤ ፍሬም ያፈራል፤ ታላቅም ዝግባ ይሆናል፤ በበታቹም ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል፤ ቅርንጫፉም ይሰፋል።
ተመልሳችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞራውያን ተራራ፥ ወደ አረባም ሀገሮች ሁሉ፥ በተራራውም፥ በሜዳውም፥ በሊባም፥ በባሕርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ፥ ተራራማውን ሀገር፥ ደቡቡንም፥ ቆላውንም፥ ቍልቍለቱንም፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
እግዚአብሔርም አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፤ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም።
በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተራራማውም ሀገር የሚኖሩ ኤናቃውያንን ከኬብሮንና ከዳቤር፥ ከአናቦትም፥ ከእስራኤልም ተራራ ሁሉ፥ ከይሁዳም ተራራ ሁሉ አጠፋቸው፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።
በተራራና በሜዳ በዓረባ፥ በአሴዶት በቆላው፥ በናጌብ፥ በኬጤዎንና በአሞሬዎን፥ በከናኔዎንና በፌርዜዎን፥ በኢያቡሴዎንና በኤዌዎን ያለ ርስታቸውን አወረሳቸው።
እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በሜዳውም በታላቁ ባሕር ዳር በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥት ሁሉ፥ ኬጤዎናዊዉ፥ አሞሬዎናዊዉም፥ ከነዓናዊዉም፥ ፌርዜዎናዊዉም፥ ኤዌዎናዊዉም፥ ኢያቡሴዎናዊዉም፥ ጌርጌሴዎናዊዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥