La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቹ​ንም ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤ ሰዎ​ቹን ሁሉ ግን እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያለ​ው​ንም ሁሉ አን​ድም አላ​ስ​ቀ​ሩም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን ምርኮውን በሙሉ፣ ከእነዚህም ከተሞች የተገኙትን እንስሳት ለራሳቸው ወሰዱ፤ ሕዝቡን ግን በሙሉ በሰይፍ ስለት ፈጁት፤ እስትንፋስ ካለው ፍጡር አንድም ሰው ሳያስቀር ፈጽመው ደመሰሱት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእስራኤል ሕዝብ ዋጋ ያለውን ንብረትና ከብቱን ሁሉ ከእነዚህ ከተሞች ወስደው የራሳቸው ንብረት አደረጉት፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ፤ አንድ ሰው እንኳ ሳይቀር ሁሉንም ገደሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፥ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም።

Ver Capítulo



ኢያሱ 11:14
12 Referencias Cruzadas  

ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥና ሕዝ​ቡም ምርኮ ይወ​ስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብ​ትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብ​ስም፥ እጅ​ግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረ​ኩ​ትም፤ ምር​ኮ​ውም ብዙ ነበ​ርና ምር​ኮ​ውን እየ​ሰ​በ​ሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።


የም​ድ​ያ​ም​ንም ሴቶ​ችና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ማረኩ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን፥ ንብ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና ኀይ​ላ​ቸ​ውን በዘ​በዙ።


ከሴ​ቶ​ቹና ከጓዙ በቀር እን​ስ​ሶ​ቹን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ያለ​ውን ምርኮ ሁሉ ዘር​ፈህ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የጠ​ላ​ቶ​ች​ህን ምርኮ ትበ​ላ​ለህ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።


እን​ዲ​ሁም ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር፥ ደቡ​ቡ​ንም፥ ቆላ​ው​ንም፥ ቍል​ቍ​ለ​ቱ​ንም፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ መታ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘ​ውም ነፍስ ያለ​በ​ትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሰዎች ሁሉ በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሳያ​ስ​ቀሩ ሁሉ​ንም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ አሶ​ር​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤


ከአ​ቃ​ጠ​ሏት ከአ​ሶር ብቻ በቀር እስ​ራ​ኤል በየ​አ​ው​ራ​ጃ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን ሌሎች ከተ​ሞች ሁሉ አላ​ቃ​ጠ​ሉም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዩን ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ ሙሴ ኢያ​ሱን አዝ​ዞት ነበር፤ ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ካዘ​ዘው ሁሉ ምንም አላ​ስ​ቀ​ረም።


በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥዋ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የከ​ብ​ቱን ምርኮ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ትዘ​ር​ፋ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በስ​ተ​ኋላ ይከ​ብ​ቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዳ​ዘ​ዘው የዚ​ያ​ችን ከተማ ከብ​ትና ምርኮ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤