La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ ግን አት​ዘ​ግዩ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እስከ መጨ​ረ​ሻው ተከ​ታ​ት​ላ​ችሁ ያዙ​አ​ቸው፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ገቡ ከል​ክ​ሉ​አ​ቸው፤” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጠላቶቻችሁን አሳድዷቸው እንጂ ችላ አትበሉ፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም አደጋ ጣሉባቸው፤ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሏቸው፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ ግን አትዘግዩ፥ ጠላቶቻችሁንም አሳድዷቸው፥ ከኋላ በኩል እየተከተላችሁም ምቱአቸው፤ አምላካችሁም ጌታ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ ግን በዚያ አትቈዩ፤ ጠላትን እያሳደዳችሁ ከኋላ በኩል አደጋ መጣላችሁን ቀጥሉ፤ ሸሽተው ወደ ከተሞቻቸው እንዲገቡ መንገድ አትስጡአቸው! አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድልን ያቀዳጃችኋልና።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ ግን አትዘግዩ፥ ጠላቶቻችሁንም አባርሩአቸው፥ በኋላም ያሉትን ግደሉ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው አለ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 10:19
8 Referencias Cruzadas  

ወደ ከተ​ማም ቢገባ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ​ዚ​ያች ከተማ ገመድ ይወ​ስ​ዳሉ፤ እኛም አንድ ድን​ጋይ እን​ኳን እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ባት ድረስ ወደ ወንዙ ውስጥ እን​ስ​ባ​ታ​ለን።”


ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “አሁን አቤ​ሴ​ሎም ከአ​ደ​ረ​ገ​ብን ይልቅ የከፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ብን የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አግ​ኝቶ ከዐ​ይ​ና​ችን እን​ዳ​ይ​ሰ​ወር፥ አንተ የጌ​ታ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ወስ​ደህ አሳ​ድ​ደው” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።


“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።


ኢያ​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወደ ዋሻው አፍ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ አን​ከ​ባ​ል​ላ​ችሁ፥ ይጠ​ብ​ቋ​ቸው ዘንድ ሰዎ​ችን በዚያ አኑሩ፤


እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ኢያ​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በታ​ላቅ መም​ታት መም​ታ​ታ​ቸ​ውን በፈ​ጸሙ ጊዜ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡት ወደ ተመ​ሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥