ኢያሱ 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም አምስት ነገሥት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ተሸሸጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ዐምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ተደብቀው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህም አምስት ነገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ተሸሸጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱ አሞራውያን ነገሥታትም አምልጠው በማቄዳ ዋሻ ተደብቀው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም አምስት ነገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ተሸሸጉ። |
እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤ ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
አምስቱም የኢያቡሴዎን ነገሥት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የላኪስ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፤ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፤ ከምድያምም ፊት የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራሮችና በገደሎች ላይ ጕድጓድና ዋሻ፥ ምሽግም አበጁ።
የእስራኤልም ሰዎች ወደ እነርሱ መሄድ እንደሚያስጨንቃቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋሻና በግንብ፥ በገደልና በቋጥኝ፥ በጕድጓድም ውስጥ ተሸሸጉ።
ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ ዋሊያዎች ወደሚታደኑባቸው ዓለቶች ሄደ።
ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው። በሳኦልም ላይ ተነሥተው ይገድሉት ዘንድ አልፈቀደላቸውም፤ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።