እግዚአብሔርም ዮናስን ይውጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘዘ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ነበረ።
ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤
ጌታም ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።
ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ እንዲህ ሲል ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤
ከፈፋው ትጠጣለህ፤ ቁራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ።” ሄደም፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው አደረገ።
እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እናገራለሁ፥ በፊቱም እዋቀሳለሁ።
አቤቱ፥ ከንፈሮችን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።
አምላካችን እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ ይናገራሉ፥ በእርሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።
አቤቱ፥ በመከራዬ ጊዜ አሰብኹህ፤ በጥቂት መከራም ገሠጽኸኝ።
እስኪጠፉ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ እሄዳለሁ፤ ወደ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።