እነዚያም ሰዎች ከእግዚአብሔር ፊት እንደ ኰበለለ እርሱ ስለ ነገራቸው ዐውቀዋልና እጅግ ፈርተው፥ “ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?” አሉት።
ዮናስ 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕሩ ይታወክ ነበርና፥ ታላቅ ማዕበልም ተነሥቶ ነበርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይልልን ዘንድ እንግዲህ ምን እናድርግህ?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሕሩም ማዕበል እጅግ እየበረታ ስለ ሄደ፣ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አሉት፦ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን ምን እናድርግብህ?” ባሕሩ መናወጡን ቀጥሎ ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባሕሩም ማዕበል እየበረታ በመሄዱ መርከበኞቹ “ይህ ማዕበል ጸጥ እንዲል በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ሲሉ ጠየቁት። |
እነዚያም ሰዎች ከእግዚአብሔር ፊት እንደ ኰበለለ እርሱ ስለ ነገራቸው ዐውቀዋልና እጅግ ፈርተው፥ “ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?” አሉት።
እርሱም፥ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደ አገኛችሁ ዐውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕሩም ጽጥ ይልላችኋል” አላቸው።