ዮሐንስ 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ሲያልፍ ዕዉር ሆኖ የተወለደውን ሰው አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድ ሲያልፍም ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የሆነ ሰው አየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደውን ሰው አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ በመንገድ ሲያልፍ ዕውር ሆኖ የተወለደ ሰው አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ። |
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨናንቁት ነበር፤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረች ሴት መጣች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ለባለመድኀኒቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያድናት የቻለ ማንም አልነበረም።
ደቀ መዛሙርቱም፥ “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተወለደው በማን ኀጢኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት።
አረማውያንም እፉኝቱ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል፤ ከባሕር እንኳ በደኅና ቢወጣም በሕይወት ይኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ፍርድ አልተወውም” አሉ።