የሕዝቤ አለቆች አላወቁኝም፤ እነርሱ ሰነፎች ልጆች ናቸው፤ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፤ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
ዮሐንስ 8:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም አታውቁትም፤ እኔ ግን ኣውቀዋለሁ፤ አላውቀውም ብልም እንደ እናንተ ሐሰተኛ እሆናለሁ፤ እኔ አውቀዋለሁ ቃሉንም እጠብቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ባታውቁትም እኔ ዐውቀዋለሁ፤ አላውቀውም ብል፣ እኔም እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን አውቀዋለሁ። አላውቀውም ብል ኖሮ እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንሁ ነበር፤ ዳሩ ግን አውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ እኔ አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንኩ ነበር፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አላወቃችሁትምም፥ እኔ ግን አውቀዋለሁ። አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንሁ፤ ዳሩ ግን አውቀዋለሁ ቃሉንም እጠብቃለሁ። |
የሕዝቤ አለቆች አላወቁኝም፤ እነርሱ ሰነፎች ልጆች ናቸው፤ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፤ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
“ምላሳቸውን ለሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ልባቸውን አላቀኑም፤ የዝሙት መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ እግዚአብሔርንም አላወቁትምና።
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር የሚያውቅ የለም። ወልድ ግን ለወደደው ይገልጥለታል።”
የምትወዱኝ ብትሆኑ ትእዛዜን ጠብቁ፤ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ፥ በፍቅሩም እንደምኖር እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
እነርሱም፥ “አባትህ የት ነው?” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔን አታውቁም፤ አባቴንም አታውቁም፤ እኔንስ ብታውቁ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር” ብሎ መለሰላቸው።
እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና።
አይሁድም እንዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን፤ አብርሃም ስንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ።
በዚህም ሳልፍ ‘ለማይታወቅ አምላክ’ የሚል ጽሕፈት ያለበትን የምታመልኩበትን መሠዊያችሁን አየሁ፤ እነሆ፥ እኔ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እገልጽላችኋለሁ።
በጨለማ ውስጥ “ብርሃን ይብራ” ያለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የክብሩን ዕውቀት ብርሃን በልባችን አብርቶልናልና።
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።