La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሊገ​ለጥ ወድዶ ሳለ በስ​ውር አን​ዳች ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማንም የለ​ምና፤ አንተ ግን ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ከሆነ ራስ​ህን ለዓ​ለም ግለጥ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ራሱን ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ማንም የለምና። አንተም እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም ግለጥ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በይፋ መታወቅ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ እራስህን ለዓለም ግለጥ፤” አሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በግልጥ ለመታወቅ የሚፈልግ ሰው ሥራውን በስውር አያደርግም፤ አንተም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስታደርግ ራስህን ለዓለም ልትገልጥ ያስፈልጋል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ራሱ ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ብታደርግ ራስህን ለዓለም ግለጥ” አሉት።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 7:4
12 Referencias Cruzadas  

ሚክ​ያ​ስ​ንም ሊጠራ የሄደ መል​እ​ክ​ተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢ​ያት ሁሉ በአ​ንድ አፍ ሆነው ለን​ጉሡ መል​ካ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል​ህም እንደ ቃላ​ቸው እን​ዲ​ሆን መል​ካም እን​ድ​ት​ና​ገር እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፤


“ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር” አለው።


“ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


መል​ካም ሰው ከልቡ መል​ካም መዝ​ገብ መል​ካ​ምን ያወ​ጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝ​ገብ ክፉ ነገ​ርን ያወ​ጣል፤ ከልብ የተ​ረ​ፈ​ውን አፍ ይና​ገ​ራ​ልና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።


ወን​ድ​ሞ​ቹም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አሉት- “ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትህ የም​ት​ሠ​ራ​ውን ሥራ​ህን እን​ዲ​ያዩ ከዚህ ወጥ​ተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ።


ወን​ድ​ሞቹ ገና አላ​መ​ኑ​በ​ትም ነበ​ርና።