ዮሐንስ 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእውነት ፍርድ ፍረዱ እንጂ ለሰው ፊት በማድላት አትፍረዱ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰውን ፊት በማየት መፍረድ ትታችሁ ቅን ፍርድ ፍረዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክለኛ ፍርድ ፍረዱ እንጂ የሰውን ፊት አይታችሁ በማዳላት አትፍረዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።” |
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፣ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፣ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥
በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ፤ ማንም በክርስቶስ ያመነ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቍጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛም እንዲሁ ነንና።