ዮሐንስ 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ሙሴ ግዝረትን ሰጥቶአችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከአባቶች ናት እንጂ ከሙሴ አይደለችም፤ በሰንበትም ሰውን ትገዝሩታላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግዝረት የመጣው ከአባቶች እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ ሆኖም ሙሴ ግዝረትን ስለ ሰጣችሁ፣ በሰንበት እንኳ ሕፃን ትገርዛላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴ መገረዝን ሰጣችሁ፤ ከአባቶችም ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ በሰንበትም ሰውን ትገርዛላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ የግዝረትን ሥርዓት ሰጣችሁ፤ ይህም ሥርዓት የተገኘው፤ ከአባቶች ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ እናንተም እኮ በሰንበት ሰውን ትገርዛላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ሙሴ መገረዝን ሰጣችሁ፤ ከአባቶችም ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ በሰንበትም ሰውን ትገርዛላችሁ። |
የግዝረትንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚህም በኋላ ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛው ቀንም ገረዘው፤ እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን፥ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የቀደሙ አባቶችን ገረዙ።
እንግዲህ እንዲህ እላለሁ፦ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ይህ ኪዳን ጽኑዕ ነው፤ ከዚህም በኋላ በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኦሪት መጣች፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ልትከለክል አይደለም።