ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
ዮሐንስ 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ስለ እርሱ ብዙ አንጐራጐሩ፥ “ደግ ሰው ነው” ያሉ ነበሩ፤ ሌሎች ግን፥ “አይደለም፤ ሕዝቡን ያስታል እንጂ” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ እርሱ በሕዝቡ መካከል ብዙ ጕምጕምታ ነበር። አንዳንዶች፣ “ደግ ሰው ነው” አሉ። ሌሎች ግን፣ “የለም፤ ሕዝቡን የሚያስት ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቡም መካከል በእርሱ ምክንያት ብዙ ማንጐራጐር ነበረ፤ አንዳንዶቹ “ደግ ሰው ነው፤” ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ ሕዝቡን ያስታል እንጂ፤” ይሉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም ስለ እርሱ በሹክሹክታ ይነጋገሩ ነበር፤ አንዳንዶቹ “እርሱ ደግ ሰው ነው” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ እርሱ ሕዝቡን ያስታል” ይሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቡም መካከል ስለ እርሱ ብዙ ማንጐራጐር ነበረ፤ አንዳንዱም፦ “ደግ ሰው ነው፤” ሌሎች ግን፦ “አይደለም፥ ሕዝቡን ግን ያስታል” ይሉ ነበር። |
ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካምን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል፤ ከልብ የተረፈውን አፍ ይናገራልና።
ሁሉም ፈሩ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነሣልን፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐብኝቶአልና።”
ፈሪሳውያንም ሕዝቡ በእርሱ ምክንያት እንደ አጕረመረሙ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ ሎሌዎቻቸውን ላኩ።
ከፈሪሳውያንም አንዳንዶች፥ “ይህ ሰው ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ሰንበትን አያከብርምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢኣተኛ ሰው እንዲህ ያለ ተአምራት ማድረግ እንዴት ይችላል?” አሉ፤ እርስ በርሳቸውም ተለያዩ።