እያንዳንዱም እንደ ደንቡ የንጉሡን ሰረገላዎች ለሚስቡ ለፈረሶችና ለሰጋር በቅሎዎች ገብስና ገለባ፥ እንዲሁም ዕቃዎችን ወደ ስፍራቸው ያመጡ ነበር።
ዮሐንስ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህ ይህን ለሚያህል ሰው ምን ይበቃሉ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዐምስት ትንንሽ የገብስ እንጀራና ሁለት ትንንሽ ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ይህ ግን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ እንዴት ይዳረሳል?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ሰው ምን ይሆናል?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ነገር ግን ይህ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምን ይበቃል?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል? አለው። |
እያንዳንዱም እንደ ደንቡ የንጉሡን ሰረገላዎች ለሚስቡ ለፈረሶችና ለሰጋር በቅሎዎች ገብስና ገለባ፥ እንዲሁም ዕቃዎችን ወደ ስፍራቸው ያመጡ ነበር።
ኤልሳዕም፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰማርያ በር፥ ሁለት መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄትም በአንድ ሰቅል ይሸመታል” አለው።
ይሁዳና እስራኤል ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ስንዴንም ይሸምቱልሽ ነበር፤ ሰሊሆትንና በለሶንን፥ ዘይትንና የተወደደ ማርን፥ ርጢንንም ከአንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።
እርሱ ግን፥ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው” አላቸው፤ እነርሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ልንገዛ ካልሄድን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለንም” አሉት።
ማርያምም ጌታችን ኢየሱስ ወደ አለበት ስፍራ ደረሰችና በአየችው ጊዜ ከእግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው።
ጌታችን ኢየሱስም ያን እንጀራ ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ ከዓሣውም እንዲሁ የፈለጉትን ያህል ሰጡአቸው።
ፊልጶስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “ከእነርሱ ለእያንዳንዱ ጥቂት ጥቂት ይወስዱ ዘንድ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም።”
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸርነቱን ታውቃላችሁ፤ በእርሱ ድህነት እናንተ ባለጸጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለጸጋ ሲሆን፥ ስለ እናንተ ራሱን ድሃ አደረገ።
በላሙ ቅቤ፥ በበጉም ወተት፥ ከፍየል ጠቦትና ከላም፥ ከጊደሮችና ከበጎች ስብ ጋር፥ ከፍትግ ስንዴ ጋር መገባቸው፤ የዘለላውንም ደም የወይን ጠጅ አድርገው ጠጡ።