La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 6:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የላ​ከኝ አብ ካል​ሳ​በው በቀር ወደ እኔ መም​ጣ​ትን የሚ​ችል የለም፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ማንም ወደ እኔ መምጣት አይችልም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል የለም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የላከኝ አብ የሳበው ካልሆነ በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል ማንም የለም፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም በመጨረሻ ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 6:44
22 Referencias Cruzadas  

ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።


በውኑ ኢት​ዮ​ጵ​ያዊ መል​ኩን ወይስ ነብር ዝን​ጕ​ር​ጕ​ር​ነ​ቱን ይለ​ውጥ ዘንድ ይች​ላ​ልን? በዚያ ጊዜ ክፋ​ትን የለ​መ​ዳ​ችሁ እና​ንተ ደግሞ በጎ ለማ​ድ​ረግ ትች​ላ​ላ​ች​ሁን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሩቅ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በዘ​ለ​ዓ​ለም ፍቅር ወድ​ጄ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ በቸ​ር​ነት ሳብ​ሁህ።


በሰው ገመድ በፍ​ቅ​ርም እስ​ራት ሳብ​ኋ​ቸው፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ፊቱን በጥፊ እን​ደ​ሚ​መ​ቱት ሰው ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ ወደ እር​ሱም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ እች​ለ​ው​ማ​ለሁ።


እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።


እኔም ከም​ድር ከፍ ከፍ ካልሁ ሁሉን ወደ እኔ እስ​ባ​ለሁ።”


ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ሳ​ችሁ አታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ።


‘ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ’ ተብሎ በነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል፤ እን​ግ​ዲህ ከአ​ባቴ የሰማ ሁሉ ተምሮ ወደ እኔ ይመ​ጣል።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከአብ ካል​ተ​ሰ​ጠው በቀር ወደ እኔ መም​ጣት የሚ​ቻ​ለው የለም።”


እን​ግ​ዲህ ቃሌን ለምን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም? ቃሌን መስ​ማት ስለ​ማ​ት​ችሉ ነው።


ይህ​ንም ጸጋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልት​ቀ​በ​ሉም ነው እንጂ ልታ​ም​ኑ​በት ብቻ አይ​ደ​ለም።


በጥ​ም​ቀ​ትም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ት​ነ​ትና በሃ​ይ​ማ​ኖት ከእ​ርሱ ጋር ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።