ዮሐንስ 6:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያ ሰዎችም ጌታችን ኢየሱስ፥ ደቀ መዛሙርቱም በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስን ይፈልጉት ዘንድ በእነዚያ ታንኳዎች ገብተው ወደ ቅፍርናሆም መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም፣ ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አለመኖራቸውን እንዳወቁ፣ ኢየሱስን ፍለጋ በጀልባዎቹ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ኢየሱስ ወይም ደቀመዛሙርቱ በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ፥ እራሳቸው በጀልባዎቹ ገብተው ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በእዚያ እንደሌሉ ባዩ ጊዜ በነዚያ ጀልባዎች ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ፥ ራሳቸው በጀልባዎቹ ገብተው ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። |
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስለቅስሻል? ማንንስ ትሺያለሽ?” አላት፤ እርስዋ ግን የአትክልት ቦታ ጠባቂ መስሎአት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እንዳመጣውና ሽቱ እንድቀባው ወዴት እንደ አኖርኸው ንገረኝ” አለችው።
ወደ ታንኳም ወጡ፤ ወደ ባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆምም ሄዱ፤ እነሆም፥ ፈጽሞ ጨለማ ሆነ፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ እነርሱ ገና አልመጣም ነበር።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ተአምራት ስለ አያችሁ አይደለም።