ዮሐንስ 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን፣ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን “እኔ ነኝ! አትፍሩ!” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው። |
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቍጥር ጥቂት የነበርህ እስራኤል ሆይ፥ እኔ እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
ራሳችሁን አትደብቁ፤ ከጥንት ጀምሮ አልሰማችሁምን? አልነገርኋችሁምን? ከእኔ ሌላ አምላክ እንደ ሌለ ምስክሮች ናችሁ።”
ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስን በባሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታንኳዉ በቀረበ ጊዜም ፈሩ።