አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
ዮሐንስ 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብ ከቶ በማንም አይፈርድም፤ ፍርዱን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብ ከቶ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ይልቁንም፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም። |
አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
በእግዚአብሔር ዘንድ በሕያዋንና በሙታን ላይ ፈራጅ ሆኖ የተሾመ እርሱ እንደ ሆነ ለሕዝብ እናስተምር ዘንድ አዘዘን።
በመረጠው ሰው እጅ በዓለም በእውነት የሚፈርድባትን ቀን ወስኖአልና፤ እርሱን ከሙታን ለይቶ በማስነሣቱም ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሶአልና።”
ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ ሰዎችን በልቡናቸው የሰወሩትንና የሸሸጉትን በሚመረምርበት ጊዜ የሚናገሩትና የሚመልሱት እንደሌለ ስለሚያውቁ ነው።
መልካም ቢሆን፥ ክፉም ቢሆን በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን እንቀበል ዘንድ፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለንና።