La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አባ​ቶ​ቻ​ችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እና​ንተ ግን ይሰ​ግ​ዱ​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባው ስፍራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነው ትላ​ላ​ችሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ አይሁድ ግን ሰው መስገድ ያለበት በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ” አለችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተ ‘ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው፤’ ትላላችሁ፤” አለችው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ‘ሰዎች ሊሰግዱ የሚገባቸው በኢየሩሳሌም ነው’ ትላላችሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተ፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 4:20
20 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ።


ዳዊ​ትም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጠራ፤ ከሰ​ማ​ይም ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ በእ​ሳት መለ​ሰ​ለት፤ እሳ​ቱም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በላ።


ዳዊ​ትም፥ “ይህ የአ​ም​ላኬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ነው፤ ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ነው” አለ።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት ተገ​ልጦ እን​ዲህ አለው፥ “ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ ይህ​ንም ስፍራ ለራሴ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ቤት መር​ጫ​ለሁ።


አሁ​ንም ስሜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መር​ጫ​ለሁ፤ ቀድ​ሻ​ለ​ሁም፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም ዘወ​ትር በዚያ ይሆ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?


ነገር ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም፤ ፊቱን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅ​ንቶ ነበ​ርና።


ይህን ጕድ​ጓድ ከሰ​ጠን ከአ​ባ​ታ​ችን ከያ​ዕ​ቆብ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? እር​ሱም ልጆ​ቹም፥ ከብ​ቶ​ቹም ከእ​ርሱ ጠጥ​ተ​ዋል።”


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ አን​ተን ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​ባት ምድር ባገ​ባህ ጊዜ፥ በረ​ከ​ቱን በገ​ሪ​ዛን ተራራ፥ መር​ገ​ሙ​ንም በጌ​ባል ተራራ ታኖ​ራ​ለህ።


“ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ሕዝ​ቡን ይባ​ርኩ ዘንድ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ስም​ዖ​ንና ሌዊ፥ ይሁ​ዳና ይሳ​ኮር፥ ዮሴ​ፍና ብን​ያም።