እርሱም፥ “ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? አሁንም ወርቁንና ልብሱን፥ ተቀብለሃል፤ ለወይን ቦታ፥ ለመሰማርያ ቦታና ለዘይት ቦታ፥ ለላሞችና ለበጎች፥ ለወንዶችና ለሴቶች ባሮች ይሁንህ።
ዮሐንስ 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደሆንህ አያለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደ ሆንክ አሁን ዐወቅሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ። |
እርሱም፥ “ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? አሁንም ወርቁንና ልብሱን፥ ተቀብለሃል፤ ለወይን ቦታ፥ ለመሰማርያ ቦታና ለዘይት ቦታ፥ ለላሞችና ለበጎች፥ ለወንዶችና ለሴቶች ባሮች ይሁንህ።
ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእስራኤል ሀገር ነቢዩ ኤልሳዕ ያለ አይደለምን? በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውንና ቃልህን ሁሉ ለእስራኤል ንጉሥ እርሱ ይነግረዋል፤” አለ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህ ምንድነው?” አላቸው፤ እነርሱም እንዲህ አሉት፥ “በእግዚአብሔር ፊትና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በቃሉና በሥራው ብርቱ ነቢይና እውነተኛ ሰው ስለነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፥
ሁሉም ፈሩ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነሣልን፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐብኝቶአልና።”
የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።”
ዳግመኛም ዕዉሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ዐይኖችህን ከፍቶልሃልና” አሉት፤ እርሱም፥ “ነቢይ ነው” አላቸው።