ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
ዮሐንስ 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ክፉም ስለሆነ ሥራው እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ አድራጎቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ነገር የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ክፉ ሥራውም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ |
ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ” አለው። የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥም፥ “ንጉሥ እንዲህ አይበል” አለ።
እርስዋም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፥ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ ሳለሁ፥ ልጄን ከብብቴ ወሰደች፤ በብብቷም አስተኛችው፤ የሞተውንም ልጅዋን በእኔ ብብት አስተኛችው።
አራጣንም በአራጣ ላይ ይቀበላሉ፤ ተንኰልን በተንኰል ላይ ይሠራሉ፤ “እኔንም ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።