ሞቶ የነበረውም እንደ ተገነዘ፥ እጁንና እግሩንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰበን እንደ ተጠቀለለ ወጣ፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንግዲህስ ፍቱትና ተዉት ይሂድ” አላቸው።
ዮሐንስ 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጐንበስ ብሎም ሲመለከት በፍታዉን ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አልገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጐንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ በፍታውን ብቻ ተቀምጦ አየ፤ ወደ መቃብሩ ግን አልገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዝቅም ብሎ ሲመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን አልገባም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐንበስ ብሎም ወደ መቃብሩ ቢመለከት የከፈኑ ጨርቅ እዚያ ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አልገባም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝቅም ብሎ ቢመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ነገር ግን አልገባ። |
ሞቶ የነበረውም እንደ ተገነዘ፥ እጁንና እግሩንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰበን እንደ ተጠቀለለ ወጣ፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንግዲህስ ፍቱትና ተዉት ይሂድ” አላቸው።