እርሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል?” አለ። እርሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪማሖስም በሰርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲንም ቀደመው።
ዮሐንስ 20:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱም በአንድነት ሲሮጡ ያ ሌላዉ ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞት ወደ መቃብሩ ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱም ይሮጡ ነበር፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ጴጥሮስን ቀድሞት ከመቃብሩ ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደረሰ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱም አብረው ይሮጡ ነበር፤ ነገር ግን ሌላው ደቀ መዝሙር ከጴጥሮስ ይበልጥ ፈጥኖ ሮጠና ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርትም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ፤ |
እርሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል?” አለ። እርሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪማሖስም በሰርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲንም ቀደመው።
እነሆም፥ ወደ ቆዳው ቢጠልቅ፥ በውስጡም ቀጭን ብጫ ጠጕር ቢኖርበት፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ ቈረቈር ነው፤ የራስ ወይም የአገጭ ለምጽ ነው።
በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሽቀዳደሙ ሁሉ እንደሚፋጠኑ አታውቁምን? ለቀደመው የሚደረግለት ዋጋ አለ፤ እንዲሁ እናንተም እንድታገኙ ፈጽማችሁ ሩጡ።