በዚያም ቀን፦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በውስጡም ያለው ስብ ይፈስሳል” ብሎ ምልክት ሰጠ።
ዮሐንስ 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም መልሰው፥ “ይህን የምታደርግ ምን ምልክት ታሳያለህ?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም፣ “ይህን ሁሉ ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ የሚያረጋግጥ ምን ታምራዊ ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አይሁድ መልሰው “ይህንን ስለ ማድረግህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን፦ “አንተ ይህን ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ ምን ተአምር ታሳየናለህ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ አይሁድ መልሰው፦ ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት። |
በዚያም ቀን፦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በውስጡም ያለው ስብ ይፈስሳል” ብሎ ምልክት ሰጠ።
“ፈርዖን፦ ተአምራትንና ድንቅን አሳዩኝ ሲላችሁ፥ ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ወስደህ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባብም ትሆናለች።”
ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።
ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው ሳሉ እንዲህ ይላቸው ጀመረ ፥ “ይቺ ትውልድ ክፉ ናት፤ ምልክትም ትሻለች፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጣትም።
አይሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠይቁት ዘንድ ካህናትንና ሌዋውያንን ከኢየሩሳሌም በላኩ ጊዜ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
“እንኪያስ ክርስቶስን ካልሆንህ፥ ኤልያስንም ካልሆንህ፥ ነቢይንም ካልሆንህ ለምን ታጠምቃለህ?” ብለው ጠየቁት።
“በኢየሱስ ስም ለማንም እንዳታስተምሩ ከልክለናችሁ አልነበረምን? እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመጡብን ዘንድ ትሻላችሁን?” አላቸው።