ዮሐንስ 19:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጭፍሮችም የእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ ደፉበት፤ የቀይ ሐር መጐናጸፊያም አለበሱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወታደሮችም የእሾኽ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አደረጉ፤ ሐምራዊ ልብስም አለበሱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወታደሮቹም ከእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ አኖሩ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮችም የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ |
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ጌታችን ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐናጸፊያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላጦስም፥ “እነሆ፥ ሰውዬው” አላቸው።