La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 18:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጲላ​ጦ​ስም ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ ወጥቶ፥ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመ​ጣ​ች​ሁ​በት በደሉ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ጲላጦስ ወደ እነርሱ ወጥቶ፣ “በዚህ ሰው ላይ የምታቀርቡት ክስ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም ጲላጦስ ወደ ውጭ፥ ወደ እነርሱ ወጥቶ “በዚህ ሰው ላይ የምታቀርቡት ምን ዓይነት ክስ ነው አላቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ጲላጦስ ወደ እነርሱ ወጣና “በዚህ ሰው ላይ ያቀረባችሁት ክስ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ ጲላጦስ ወደ ውጭ ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ “ይህን ሰው ስለ ምን ትከሱታላችሁ” አላቸው።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 18:29
9 Referencias Cruzadas  

ገዢውም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ ጩኸት አበዙ።


እነ​ር​ሱም፥ “ክፉ የሠራ ባይ​ሆ​ንስ ወደ አንተ አሳ​ል​ፈን ባል​ሰ​ጠ​ነው ነበር” ብለው መለ​ሱ​ለት።


ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገብቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ጠራና፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።


እኔም፦ ተከ​ሳሹ በከ​ሳ​ሾቹ ፊት ሳይ​ቆም፥ ለተ​ከ​ሰ​ሰ​በ​ትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያ​ገኝ ማንም ቢሆን አሳ​ልፎ መስ​ጠት የሮ​ማ​ው​ያን ሕግ አይ​ደ​ለም ብየ መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።


በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።