ጴጥሮስም ደግሞ ካደ፤ ያንጊዜም ዶሮ ጮኸ።
ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።
ጴጥሮስም በድጋሚ ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።
ጴጥሮስም እንደገና ካደ፤ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ።
ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፥ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።
ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።
ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።
እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቅም፤ አላስተውልምም፤” ብሎ ካደ። ወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣ፤ ዶሮም ጮኸ።
እርሱ ግን፥ “ጴጥሮስ ሆይ፥ እልሃለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ እንደማታውቀኝ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።
እርሱ ግን፥ “ሴትዮ! የምትዪውን አላውቅም” ብሎ ካደ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ነፍስህን ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ዶሮ አይጮህም።