ዮሐንስ 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰጠኸኝም ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ ዛሬ ዐወቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ዐውቀዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃልህንም ጠብቀዋል። የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደሆነ አሁን ያውቃሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ እነርሱ አሁን ዐውቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃልህንም ጠብቀዋል። የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያውቃሉ፤ |
የሰጠኽኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀብለው ከአንተ እንደ ወጣሁ በእውነት ዐወቁ፤ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ በአደረጋችሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ፤ አባቴ እንደ አስተማረኝም እንዲሁ እናገራለሁ እንጂ የምናገረው ከእኔ አይደለም።