La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህች ወንድሟ አልዓዛር የታመመባት ማርያም፣ ጌታን ሽቱ ቀብታ እግሮቹን በጠጕሯ ያበሰችው ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጉርዋ ያበሰችው ስትሆን፤ የታመመውም አልዓዛር ወንድምዋ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህች ማርያም የጌታን እግር ሽቶ የቀባችውና በጠጒርዋ ያበሰችው ናት፤ የታመመውም አልዓዛር የእርስዋ ወንድም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 11:2
11 Referencias Cruzadas  

እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።


ጌታ​ች​ንም በአ​ያት ጊዜ አዘ​ነ​ላ​ትና፥ “አታ​ል​ቅሺ” አላት።


ዮሐ​ን​ስም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ?” ብሎ ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ላካ​ቸው።


ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር።


እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።


ማር​ያ​ምም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ አለ​በት ስፍራ ደረ​ሰ​ችና በአ​የ​ችው ጊዜ ከእ​ግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር” አለ​ችው።


ማር​ያም ግን ዋጋዉ የከ​በ​ረና የበዛ አንድ ነጥር የጥሩ ናር​ዶስ ሽቱ ወሰ​ደ​ችና የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እግር ቀባ​ችው፤ በፀ​ጕ​ሯም አሸ​ችው፤ የዚያ ሽቱ መዓ​ዛም ቤቱን መላው።


እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና።


እን​ግ​ዲህ እኔ መም​ህ​ራ​ች​ሁና ጌታ​ችሁ ስሆን እግ​ራ​ች​ሁን ካጠ​ብ​ኋ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ የባ​ል​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን እግር ልታ​ጥቡ ይገ​ባ​ች​ኋል።