ዮሐንስ 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስም፥ ባልንጀሮቹን ደቀ መዛሙርት፥ “እኛም ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እንሂድ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ለተቀሩት ደቀ መዛሙርት፣ “እኛም ሄደን ከርሱ ጋራ እንሙት” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዲዲሞስ የሚሉትም ቶማስ ለሌሎቹ ደቀ መዛሙርት “ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛም እንሂድ፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ሌሎቹን ደቀ መዛሙርት፥ “ከእርሱ ጋር እንድንሞት እኛም እንሂድ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርቱ፦ “ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ” አለ። |
ደቀ መዛሙርቱም፥ “መምህር ሆይ፥ አይሁድ ሊወግሩህ ይሹ አልነበረምን? ዛሬ ደግሞ አንተ ወደዚያ ልትሄድ ትሻለህን?” አሉት።
ጴጥሮስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን አሁን ልከተልህ አልችልም? እኔ ነፍሴንም እንኳ ቢሆን ስለ አንተ አሳልፌ እሰጣለሁ” አለው።
ስምዖን ጴጥሮስ፥ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ፥ ከገሊላ ቃና የሆነው ናትናኤል፥ የዘብዴዎስ ልጆችና ሌሎችም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት አብረው ነበሩ።
ወደ ማደሪያቸውም በደረሱ ጊዜ ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴዎስ፥ በርተሎሜዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖን፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ።