ከዚህም በኋላ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ አብረውት ካሉት ከነገሥታቱ ሁሉ ጋር በድንኳኑ ውስጥ ይጠጣ ነበር፤ አገልጋዮቹንም፥ “ከተማውን እጠሩት” አላቸው። እነርሱም በከተማዪቱ ትይዩ ተሰለፉ።
ኢዩኤል 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጽዮን መለከትን ንፉ፤ ጾምንም ቀድሱ፤ ምህላንም ዐውጁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጽዮን መለከትን ንፉ፤ ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤ የተቀደሰን ጉባኤ ጥሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጽዮን ተራራ ላይ መለከት ንፉ! ሕዝቡን ለመንፈሳዊ ስብሰባ ጥሩ! ጾምንም ዐውጁ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥ |
ከዚህም በኋላ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ አብረውት ካሉት ከነገሥታቱ ሁሉ ጋር በድንኳኑ ውስጥ ይጠጣ ነበር፤ አገልጋዮቹንም፥ “ከተማውን እጠሩት” አላቸው። እነርሱም በከተማዪቱ ትይዩ ተሰለፉ።
ለወልደ አዴር መልእክተኞችም፥ “ለጌታችሁ፦ ለእኔ አገልጋይህ በመጀመሪያ የላክህብኝን ሁሉ አደርጋለሁ፤ ይህን ነገር ግን አደርገው ዘንድ አይቻለኝም” በሉት አላቸው። መልክእክተኞችም ተመልሰው ይህን ነገር ነገሩት።
መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን አልወድም።
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም ዐዋጅ ነገሩ።
ጾምን ቀድሱ፤ ምህላንም ዐውጁ፤ ሽማግሌዎቹንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ጩኹ።
በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና።