La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የመ​ር​ከብ መን​ገድ ፍለጋ፥ ወይም የሚ​በ​ርና የሚ​በ​ላ​ውን የሚ​ፈ​ልግ የን​ስር ፍለጋ እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ ሕይ​ወቴ እን​ዲሁ ሆነ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ፣ ለመንጠቅ ቍልቍል እንደሚበርር ንስር ይፈጥናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ ይሮጣሉ፤ እንደ ነጣቂ ንስርም ይፈጥናሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋል።

Ver Capítulo



ኢዮብ 9:26
8 Referencias Cruzadas  

ሳኦ​ልና ዮና​ታን የተ​ወ​ደ​ዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውና በሞ​ታ​ቸው አል​ተ​ለ​ያ​ዩም፤ ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ ከአ​ን​በ​ሳም ይልቅ ብር​ቱ​ዎች ነበሩ።


በእርሱ ላይ ዐይንህን ብታተኩር አታገኘውም፥ ለእርሱ የንስር ክንፍ ተዘጋጅቶለታልና። ወደሚቆምበትም ቤት ይመለሳልና።


መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በባ​ሕር ላይ፥ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ች​ንም በውኃ ላይ ይል​ካል። ፈጣ​ኖች መል​እ​ክ​ተ​ኞች ወደ ረዥ​ምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄ​ዳ​ሉና፤ ተስፋ የቈ​ረ​ጡና የተ​ረ​ገጡ ሕዝብ እነ​ማን ናቸው? ዛሬ ግን የም​ድር ወን​ዞች ሁሉ፥ ሰዎች እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ሀገር ይኖ​ራሉ።


እነሆ! እንደ ደመና ይወ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረ​ሶ​ቹም ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ናቸው። ተዋ​ር​ደ​ና​ልና ወዮ​ልን።


ቆፍ። አሳ​ዳ​ጆ​ቻ​ችን ከሰ​ማይ ንስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ሆኑ፤ በተ​ራ​ሮች ላይ አሳ​ደ​ዱን፤ በም​ድረ በዳም ሸመ​ቁ​ብን።


ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፣ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥