ኢዮብ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድንጋይ ክምር ላይ ያድራል፤ በድንጋዮቹም መካከል ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥሩን በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጥማል፤ በዐለትም መካከል ስፍራ ያበጃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፥ የድንጋዩቹን ቦታ ይመለከታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥሮቹም በድንጋይ ካብ ላይ ይጠመጠማሉ፤ በየቋጥኙም ላይ ይጣበቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፥ የድንጋዩቹን ቦታ ይመለከታል። |
በእርሱም ላይ ዛፉንና ሣሩን፥ የማይቈጠር ሌላውንም ብዙ ፍጥረት የፈጠረ እርሱ ነው። ነፋስም በነፈሰባቸው ጊዜ ይደርቃሉ፤ ዐውሎ ነፋስም እንደ ገለባ ይጠርጋቸዋል።
ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥