ኢዮብ 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተኛሁም ጊዜ፦ መቼ ይነጋል? እላለሁ፤ በተነሣሁም ጊዜ ዳግመኛ መቼ ይመሻል? እላለሁ፤ ከማታ እስከ ጥዋት ድረስ መከራን ጠገብሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተኛሁ ጊዜ ‘መቼ ነግቶ እነሣለሁ?’ እላለሁ፤ ሌሊቱ ይረዝማል፤ እስኪነጋም እገላበጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? እላለሁ። ሌሊቱ ግን ይረዝማል፥ እስኪ ነጋ ድረስም እገለባበጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምተኛበት ጊዜ መቼ እነሣ ይሆን ብዬ አስባለሁ፤ ሌሊቱ ግን ይረዝምብኛል፤ እኔም እስኪነጋ ድረስ ስገላበጥ ዐድራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? እላለሁ። ሌሊቱ ግን ይረዝማል፥ እስኪነጋ ድረስም እገለባበጣለሁ። |
አንቺ የተቸገርሽ የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን የሚያበሩ አደርጋለሁ፤ መሠረትሽንም የሰንፔር አደርገዋለሁ።
ከፈራህበት ከልብህ ፍርሀት የተነሣ፥ በዐይንህም ካየኸው የተነሣ፥ ሲነጋ እንዴት ይመሽ ይሆን? ትላለህ፤ ሲመሽም እንዴት ይነጋ ይሆን? ትላለህ።