ኢዮብ 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ እኔ የከንቱ ወራትን ታገሥሁ፥ የፃዕርም ሌሊት ተወሰነችልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁ ከንቱ ወራት ታደሉኝ፣ የጕስቍልና ሌሊቶችም ተወሰኑልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥ የድካምም ሌሊት ተወሰነችልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የድካም ወሮቹ ለእኔ ጥቅም የለሽ ሆኑ፤ የችግር ሌሊቶቹም ለእኔ የጭንቅ ሌሊት ሆኑብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥ የድካምም ሌሊት ተወሰነችልኝ። |
ወይም ጌታውን እንደሚፈራ አገልጋይ ጥላውንም እንደሚመኝ፥ ወይም ደመወዙን እንደሚጠብቅ ምንደኛ አይደለምን?
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።