ኢዮብ 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከተሞችና በገንዘቦች የሚታመኑ ያፍራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርግጠኞች ሆነው ስለ ነበር ተሰቀቁ፤ እዚያ ደረሱ፣ ግን ዐፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተስፋ አድርገውባቸው ነበርና አፈሩ፥ ወደዚያ ደረሱ፥ እፍረትም ያዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተማመኑበትን ወንዝ ደርቆ ሲያገኙ ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ወደ ቦታውም ሲደርሱ ይበሳጫሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተስፋ አድርገዋቸው ነበርና አፈሩ፥ ወደዚያ ደረሱ፥ እፍረትም ያዛቸው። |
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።
አቤቱ! የእስራኤል ተስፋ ሆይ! የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።
መጽሐፍ እንዲሁ “በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይንና የማሰናከያ ዐለትን አኖራለሁ፤ ያመነባትም ለዘለዓለም አያፍርም” ብሎአልና።