ኢዮብ 5:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘርህም ብዙ እንዲሆን፥ ልጆችህም እንደ አማረ መስክ ሣር እንዲሆኑ ታውቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሮችህ አያሌ እንደሚሆኑ፣ የምትወልዳቸውም እንደ ሣር እንደሚበዙ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘርህም እንደሚበዛ፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር ብዙ እንደሚሆን ታውቃለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትውልድህ እንደሚበዛ ታውቃለህ፤ ዘርህም እንደ መስክ ሣር ይበዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘርህም ታላቅ እንዲሆን፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር እንዲሆን ታውቃለህ። |
ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው።
ወደ እናንተም እመለከታለሁ፤ አባዛችኋለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርጋችኋለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።