ኢዮብ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምላስ ጅራፍ ይሰውርሃል፥ ከምትመጣብህም ክፋት አትፈራም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ ጥፋት ሲመጣም አትፈራም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፥ የጥፋት አደጋ ሲመጣም አትፈራም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከክፉ ምላስ ይጠብቅሃል፤ ጥፋት ቢመጣብህም አትፈራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፥ ጥፋትም ሲመጣ አትፈራም። |
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ እንዲከናወን አላደርግም፤ በአንቺ ላይ ለፍርድ የሚነሣውን ድምፅ ሁሉ ታጠፊያለሽ፤ ጠላቶችሽም ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ እግዚአብሔርንም ለሚያገለግሉ ርስት አላቸው፤ ጻድቃኔም ትሆኑኛላችሁ ይላል እግዚአብሔር።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።