ኢዮብ 41:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡ እንደ ዋሻ ድንጋይ የደነደነ ነው፤ እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጸና ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጀርባው፣ አንድ ላይ የተጣበቁ፣ የጋሻ ረድፎች አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋውም እርስ በርስ የተጣበቀ ነው፥ ምንም ላያንቀሳቅሳቸው በእርሱ ላይ ጸንተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጀርባው ቆዳዎች በመደዳ እንደ ተደረደሩ ጋሻዎች ናቸው፤ እጅግ የተጣበቁም ስለ ሆኑ እንደ ብረት ጠንካሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሥጋውም ቅርፊት የተጣበቀ ነው፥ እስከማይንቀሳቀሱም ድረስ በእርሱ ላይ ጸንተዋል። |
ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።