“በመቃብር ውስጥ ምነው በጠበቅኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪበርድም ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! እስከምታስበኝም ምነው ቀጠሮ በሰጠኸኝ ኖሮ!
ኢዮብ 40:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፤ ፊታቸውንም በኀፍረት ሙላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉንም በአንድ ላይ ከዐፈር ደባልቃቸው፤ ፊታቸውንም በመቃብር ውስጥ ሸፍን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፥ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከፈን ጨርቅም ጠቅልለህ ሁሉንም በአንድነት በመሬት ውስጥ ቅበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፥ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን። |
“በመቃብር ውስጥ ምነው በጠበቅኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪበርድም ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! እስከምታስበኝም ምነው ቀጠሮ በሰጠኸኝ ኖሮ!
አሁንም ምድርን ያነዋውጣት ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመሬት ውስጥም ተሸሸጉ።
ሞቶ የነበረውም እንደ ተገነዘ፥ እጁንና እግሩንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰበን እንደ ተጠቀለለ ወጣ፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንግዲህስ ፍቱትና ተዉት ይሂድ” አላቸው።