ኢዮብ 39:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀንበር ትጠምደዋለህን? በእርሻህስ ውስጥ ትልም ያርስልሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ? ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጕልልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐሽ እንዲተልምልህ ልታጠምደው ትችላለህን? ወይስ ከአንተ በኋላ በእርሻ ላይ ይጐለጉላልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐሽን ጠምደህ ሞፈር እየጐተተ እንዲያርስ ልታደርገው ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጐሽ ይተልምልህ ዘንድ ትጠምደዋለህን? ወይስ ከአንተ በኋላ በእርሻ ላይ ይጐለጕላልን? |
በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፥ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፥ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።