ኢዮብ 38:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናውን በቃልህ ትጠራዋለህን? ብዙ ውኃስ እየተንቀጠቀጠ ይመልስልሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣ ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የውኆች ሙላት ይሸፍንህ ዘንድ። ቃልህን ወደ ደመናት ታነሣ ዘንድ ትችላለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ብዙ ዝናብ እንዲያዘንብልህ፥ ደመናን ልታዘው ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የውኆች ብዛት ይሸፍንህ ዘንድ። ቃልህን ወደ ደመናት ታነሣ ዘንድ ትችላለህን? |
ሁሉን የሚሠራና የሚያቅናና፥ ብርሃኑን ወደ መስዕ የሚመልሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚያጨልመው፥ የባሕሩንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ነው።
በኋለኛው ዝናብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዝናቡን ለምኑ፣ እግዚአብሔር መብረቅ ያደርጋል፣ እርሱም የበልግ ዝናብን ለእያንዳንዱም በሜዳ ውስጥ ሣርን ይሰጣል።
ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም በዚያ ቀን ነጐድጓድንና ዝናብን ላከ፤ ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩአቸው።