La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 37:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በስ​ተ​ኋ​ላው ድምፅ ይጮ​ኻል፤ በግ​ር​ማ​ውም ድምፅ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ድም​ፁም በተ​ሰማ ጊዜ ሰዎች እን​ዲ​ጠፉ አያ​ደ​ር​ግም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤ በድምፁም ግርማ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁ በተሰማ ጊዜ፣ መብረቁን የሚከለክል የለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከበስተኋላው ድምፅ ያገሣል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጉዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።

Ver Capítulo



ኢዮብ 37:4
12 Referencias Cruzadas  

እነሆ ይህ የመ​ን​ገዱ ክፍል ነው፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ነገ​ሮ​ቹን እን​ሰ​ማ​ለን፤ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በ​ትስ ጊዜ የነ​ጐ​ድ​ጓ​ዱን ኀይል የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?”


እነ​ዚ​ህን በፈ​ጠረ ጊዜ እን​ዲሁ ዐውቆ ቈጠ​ራ​ቸው። ለዝ​ናም ሥር​ዐ​ትን ለነ​ጐ​ድ​ጓድ መብ​ረ​ቅም መን​ገ​ድን አደ​ረገ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቍ​ጣ​ውን ድምፅ ስማ፥ ከአ​ፉም የሚ​ወ​ጣ​ውን ጕር​ም​ር​ምታ አድ​ምጥ።


እር​ሱን ወደ ሰማ​ያት ሁሉ ታች፥ ብር​ሃ​ኑ​ንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰ​ድ​ዳል።


ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ምፁ ድንቅ አድ​ርጎ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ለእ​ን​ስ​ሳት በየ​ጊ​ዜው ምግ​ባ​ቸ​ውን ያዘ​ጋ​ጃል፥ የሚ​ተ​ኙ​በ​ት​ንም ጊዜ ያው​ቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይ​ደ​ን​ግ​ጥ​ብህ፤ ሥጋ​ህም ልብ​ህም ከግ​ዘፉ አይ​ለ​ወ​ጥ​ብህ፤ እር​ሱም እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን ታላቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክንድ ያለ ክንድ አለ​ህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታን​ጐ​ደ​ጕ​ዳ​ለ​ህን?


የአ​ን​ደ​በቴ ቃል ያማረ ይሁን፤ የልቤ ዐሳ​ብም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው አቤቱ ረድ​ኤቴ መድ​ኀ​ኒ​ቴም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።