ኢዮብ 32:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ንግግሬን አድምጡኝ፤ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ እየሰማችሁት እነግራችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በምትነጋገሩበት ጊዜ ታገሥሁ፤ ቃላት እየመረጣችሁ ስትናገሩ፣ በጥሞና ሰማኋችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ ሙግታችሁን አዳመጥሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ የምታቀርቡትን ምክንያት እጠባበቅ ነበር። ሐሳባችሁን ግልጥ ለማድረግ ቃላት በመምረጥ፥ የምትናገሩትንም አዳምጥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ ብልሃታችሁን አዳመጥሁ። |