“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ ለመዘባበት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባቶቻቸውን የናቅሁባቸውና እንደ መንጋዬ ውሾች ያልቈጠርኋቸው ዛሬ ለብቻቸው ይገሥጹኛል።
ኢዮብ 30:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምንድን ነው? ሞት በላያቸው ይምጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልበት የከዳቸው፣ የክንዳቸው ብርታት ምን ፋይዳ ይሞላልኝ ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀድሞ ጥንካሬአቸው ጠፍቶ ነበርና የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይጠቅማል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይላቸው የደከመ ስለ ነበረ፥ ለእኔ ምንም አይጠቅሙኝም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሉ ሰው መሆናቸው ጠፍቶባቸው ነበርና የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይጠቅማል? |
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ ለመዘባበት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባቶቻቸውን የናቅሁባቸውና እንደ መንጋዬ ውሾች ያልቈጠርኋቸው ዛሬ ለብቻቸው ይገሥጹኛል።