La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 30:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አሁን ግን በዕ​ድሜ ከእኔ የሚ​ያ​ንሱ ለመ​ዘ​ባ​በት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን የና​ቅ​ሁ​ባ​ቸ​ውና እንደ መን​ጋዬ ውሾች ያል​ቈ​ጠ​ር​ኋ​ቸው ዛሬ ለብ​ቻ​ቸው ይገ​ሥ​ጹ​ኛል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፣ ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጋራ እንዳይቀመጡ፣ አባቶቻቸውን የናቅኋቸው፣ እነዚህ ይሣለቁብኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ውሾች ጋር ለማኖር የናቅኋቸው፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ ያነሱ ሰዎች ያፌዙብኛል፤ የእነርሱ አባቶች የበጎቼን መንጋ ከሚጠብቁ ውሾቼ ጋር እንኳ እንዲሰማሩ የምንቃቸው ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ውሾች ጋር ለማኖር የናቅኋቸው፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 30:1
17 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመ​ን​ገ​ድም ሲወጣ ልጆች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጥ​ተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌ​ዙ​በት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጠ​ራሁ እር​ሱም የመ​ለ​ሰ​ልኝ እኔ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው መሣ​ለ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ሆን ሰው ሆኛ​ለሁ፤ ጻድ​ቁና ንጹሑ ሰው መሣ​ለ​ቂያ ሆኖ​አል።


የእ​ጃ​ቸው ብር​ታት ለእኔ ምን​ድን ነው? ሞት በላ​ያ​ቸው ይምጣ።


ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይገ​ፋ​ፋል፤ ብላ​ቴ​ና​ውም በሽ​ማ​ግ​ሌው ላይ፥ የተ​ጠ​ቃ​ውም በከ​በ​ር​ቴው ላይ ይታ​በ​ያል።


አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና “ትንቢት ተናገር፤” ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ሰው ሕዝ​ብን ያሳ​ም​ፃል ብላ​ችሁ ወደ እኔ አመ​ጣ​ች​ሁት፤ በፊ​ታ​ች​ሁም እነሆ፥ መረ​መ​ር​ሁት፤ ግን እና​ንተ ካቀ​ረ​ባ​ች​ሁት ክስ በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ዳች በደል የለም።


ሁሉም በሙሉ፥ “ይህን አስ​ወ​ግ​ደው፥ ስቀ​ለ​ውም፥ በር​ባ​ንን ግን ፍታ​ልን” ብለው ጮሁ።


ሕዝ​ቡም ቆመው ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ አለ​ቆ​ችም፥ “ሌሎ​ችን አዳነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ክር​ስ​ቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌ​ዙ​በት ነበር።


አብ​ረው ተሰ​ቅ​ለው ከነ​በ​ሩት አንዱ ወን​በዴ፥ “አን​ተስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ንህ ራስ​ህን አድን፤ እኛ​ንም አድ​ነን” ብሎ ተሳ​ደበ።


የማ​ያ​ምኑ አይ​ሁድ ግን ቀኑ​ባ​ቸው፤ ከገ​በ​ያም ክፉ​ዎች ሰዎ​ችን አም​ጥ​ተው፥ ሰዎ​ች​ንም ሰብ​ስ​በው ሀገ​ሪ​ቱን አወ​ኳት፤ ፈለ​ጓ​ቸ​ውም፤ የኢ​ያ​ሶ​ንን ቤትም በረ​በሩ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ሊያ​ወ​ጧ​ቸው ሽተው ነበር።


የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው፤” ብሎአል።