ኢዮብ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያች ቀን ጨለማ ትሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከታት፥ ብርሃንም አይብራባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ ብርሃንም አይብራበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያ ቀን ጨለማ ይሁን፥ እግዚአብሔር ከላይ አይፈልገው፥ ብርሃንም አይብራበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ቀን ወደ ጨለማ ይለወጥ፤ የሰማይ አምላክ አያስበው፤ ብርሃን ከቶ አይታይበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ ቀን ጨለማ ይሁን፥ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት። |
የጨለማና የነፋስ ቀን፥ የደመናና የጉም ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘለዓለምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አልነበረም፤ ከእርሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም።
የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።
አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት ሀገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእርስዋ ላይ ነው።